መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጋብቻ ምን ይላል
ስለ ጋብቻ 5 ክፍሎች፣ ከዕብራይስጥና ከግሪክኛ የተተረጎሙ።
እነዚህ ክፍሎች በAI እርዳታ የተመረጡ ናቸው፤ ገና በስም በተጠቀሰ ገምጋሚ አልተረጋገጡም።
ዘፍጥረት 2:24
ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣበቃል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ።
ኤፌሶን 5:25
ባሎች ሆይ፣ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደደና ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ ሚስቶቻችሁን ውደዱ።
ማርቆስ 10:9
እንግዲያውስ እግዚአብሔር በአንድ ቀንበር ያጣመረውን ማንም ሰው አይለየው።»
ዕብራውያን 13:4
ሁላችሁም ጋብቻን አክብሩ፤ የጋብቻንም መኝታ ከርኩሰት ጠብቁ፤ እግዚአብሔር በዝሙተኞችና ለትዳራቸው ታማኝ ባልሆኑት ላይ ይፈርዳልና።
መክብብ 4:9–12
ሁለት ከአንድ ይሻላሉ፤ አብረው ስለ ድካማቸው መልካም ዋጋ ያገኛሉና። አንዱ ቢወድቅ ሌላው ሊያነሣው ይችላል። ብቻውን ሆኖ ለሚወድቅና የሚያነሣው ለሌለው ግን ወዮለት! ደግሞም ሁለት ሰዎች አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ አንዱ ብቻውን ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል? አንድ ሰው ብቻውን ሊሸነፍ ይችላል፤ ሁለት ሰዎች ግን በአንድነት አጥቂውን ሊቋቋሙት ይችላሉ፤ በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች
ጓደኝነት · ቤተ ክርስቲያን · የፆታ ንጽሕና · ፍቺ · ዝሙት · ገንዘብ · ልጆች · ምስጋና · ሥራ · ብቸኝነት