Open Word Bible

የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እንቅልፍ ምን ይላል

ስለ እንቅልፍ 5 ክፍሎች፣ ከዕብራይስጥና ከግሪክኛ የተተረጎሙ።

እነዚህ ክፍሎች በAI እርዳታ የተመረጡ ናቸው፤ ገና በስም በተጠቀሰ ገምጋሚ አልተረጋገጡም።

  1. መዝሙር 4:8

    በሰላም እተኛለሁ፤ ወዲያውም እንቅልፍ ይወስደኛል፤ እግዚአብሔር ሆይ፣ በደኅንነት እንድኖር የምታደርገኝ አንተ፣ አንተ ብቻ ነህና።

    በዐውዱ ያንብቡ →

  2. መዝሙር 127:2

    በማለዳ መነሣታችሁ፣ እስከ ሌሊት መቆየታችሁ፣ በጭንቀት ሥራ ያገኛችሁትን እንጀራ መብላታችሁ ምንም አይጠቅማችሁም፤ እርሱ ለሚወደው እንቅልፍን ይሰጠዋል።

    በዐውዱ ያንብቡ →

  3. ምሳሌ 3:24

    ወደ መኝታህ ስትሄድ የምትፈራው ነገር አይኖርም፤ ትተኛለህ፤ በሰላምም ታንቀላፋለህ።

    በዐውዱ ያንብቡ →

  4. መዝሙር 3:5

    ተኛሁ፤ እንቅልፍም ወሰደኝ፤ እንደ ገናም ነቃሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና።

    በዐውዱ ያንብቡ →

  5. መዝሙር 121:3–4

    እግርህ እንዲሰናከል ከቶ አይተው፤ የሚጠብቅህም ከቶ አያንጎላጅ። በእርግጥም እስራኤልን የሚጠብቀው ከቶ አያንጎላጅም፤ እንቅልፍም አይወስደውም።

    በዐውዱ ያንብቡ →

የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች

ዕረፍት · ልጆች · ጥበብ · ልጅ አስተዳደግ · እግዚአብሔርን መታመን · ጤና · ዓመፅ · የእግዚአብሔር ጥበቃ · በማኅፀን ያለ ሕፃን · ታማኝነት